Uncategorized

ወጣቱ ትውልድ ሰላምን እያፀና የተጀመሩ ልማቶች ዳር እንዲደርሱ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፦ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው

ወጣቱ ትውልድ ሰላምን እያፀና የተጀመሩ ልማቶች ዳር እንዲደርሱ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፦ ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው

የጎንደር ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳይ ከጎንደር ከተማ ወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው እንደገለጹት የከተማዋን ልማት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።

ጎንደር አሁን ወደ ቀደመ ገናና ክብሯ ለመመለስ በትኩረት እየተስራ መሆኑን ገልጸዋል ።

ከጎንደር ከተማ የሚተሳሰረው የጎርጎራ ልማት ፣ የጎንደር መካነ ቅርስ ጥገና ፣ የውሃ መሰል ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የከተማ ልማት ስራዎች የአሁኗ ጎንደር መገለጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል ።

የለውጡ መንግስት ኢትዮጵያን ለማበልፀግ እየሄደባቸው ያላቸው መንገዶች ሁሉ ለጎንደር መልካም እድል ይዘው የመጡ መሆናቸውን የጠቀሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው በጎንደር መፃኢ ዕድሎች ላይ ብሩህ ተስፋን የፈነጠቀ መሆኑን አመላክተዋል ።

ከተማዋን የኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስት ቅርስ ጥገናን ተከትሎ በቀንና በማታ ለመጎብኘት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል ።

የተጀመሩ ልማቶች ዳር እንዲደርሱ የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል ። የተጀመሩ ልማቶች በአጠር ጊዜ እንዲጠናቀቁ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል ።

ትውልድ ግንባታ ላይ በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልፀው የትምህርት ቤት ደረጃ የማሻሻል እና የተማሪዎች ምገባ ላይ በጋራ እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ለከተማው ሰላም ወጣቱ አጋዥ መሆን እንደሚገባቸው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል ።

የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኃላ ደግሞ የጎንደር ከተማ ወጣቶች አሁን ላላው ሰላም ድርሻቸው ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

በዚህ ዓመት በርካታ ፕሮጀክቶች በከተማው መከናወኑን ጠቅሰው ከተማዋን ለማዘመን አበረታች ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል ። ለኮሪደር ልማቱ የከተማው ህዝብ አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑንም አብራርተዋል ።

የስራ እድል ፈጠራ ውጤታማ ስራ ለመስራት ወጣቱ የአካባቢውን ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን የጀመረውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

ለጋራ ሀገራችን በጋራ በመቆም ለከተማው ሰላምና ልማት በጋራ እንስራ ሲሉ ወይዘሮ ደብሬ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

አሁን ያለውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ተሟላ ሰላም ለመቀየር ወጣቱ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የጎንደር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሪት ናርዶስ ቢራራ ገልጸዋል ።

የኢንቨስትመንቱ ፍሰቱን የበለጠ ለማሳደግ እና ወጣቱን በልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ሰላም አስፈላጊ በመሆኑ ወጣቱ ለሰላም ከመንግሰት ጎን በመሰለፍ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አስረድተዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ፡ በከተማው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች መሆኑን ጠቅሰው የአካባቢን ሰላም ለመጠበቅ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስተያየታቸውን ስጥተዋል።

የሚፈለገውን ብልፅግና ለማረጋገጥ ከመንግሥት ጎን በመቆም ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል ።

Leave A Comment

Your Comment
All comments are held for moderation.