በአማራ ክልል በግማሽ ዓመቱ አምራቾች ኢንዱስትሪዎች 297 ሺህ ቶን ተኪ ምረት በማምረት ወደ ወጭ ሊወጣ የነበረውን 333 ሚሊዮን ዶላር ማትረፍ መቻሉን ተገለፀ።
በአማራ ክልል በግማሽ ዓመቱ አምራቾች ኢንዱስትሪዎች 297 ሺህ ቶን ተኪ ምረት በማምረት ወደ ወጭ ሊወጣ የነበረውን 333 ሚሊዮን ዶላር ማትረፍ መቻሉን ተገለፀ።
የክልልና የከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ ወደ ምርት የገቡ አምራች ኢንዱስትሪዎችንና ማሽን ተከላ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በክልሉ 85 መካከለኛ እና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ማስገባታቸውን በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ ገልጸዋል ።
አምራቾች ኢንዱስትሪዎች 297 ሺህ ቶን ተኪ ምረት በማምረት ወደ ወጭ ሊወጣ የነበረውን 333 ሚሊዮን ዶላር ማትረፍ መቻሉን ተናግረዋል ።
በክልሉ በግማሽ ዓመቱ በኢንቨስትመንት በየተሰማሩ ባለ ሀብቶች ለ43ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ኃላፊው ገልጸዋል ።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኃላ በከተማው በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ወደ ስራ ያልገቡ ወደ ስራ ለማስገባት እና ወደ ስራ የገቡት ደግሞ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ የመስክ መልከታ ማድረጋቸውን ገልጸዋል ።
ማሽን ተከላ እና ምርት ማምረት የጀመሩ አምራቾች ኢንዱስትሪዎች መመልከታቸው የጠቀሱት ምክትል ከንቲባዋ ገበታ ዘይት ፋብሪካ ምርት በማምረት ገቢያን በማረጋጋት የድርሻውን እየተወጣ ያለ ድርጀት መሆኑን ገልጸዋል ።
ኤርፎራ ለረዥም ጊዜ ተዘግቶ የቆይ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ ማሽን ተከላ ላይ ያለ መሆኑን ተናግረዋል ።
ድርጅቱ ወደ ስራ ሲገባ ለበርካታ ዜጎችን የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው በአካባቢው በእንሰሳት ሀብት ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚነታቸውን ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል ።
ለአካባቢው አርሶ አደሮችም ተጠቃሚታቸውን ለማረጋገጥ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል ።
ባለሀብቶች የሚያነሱት የነዳጅ ና የብድር አቅርቦት ጥያቄዎች ከተማ አስተዳደሩ ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት ለመፍታት የተደረገ የመስክ ጉብኝት መሆኑን አስረድተዋል ።
ስራ ፈላጊዎች ወደ ስራ ለማስገባት ኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የኤርፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ጎንደር ኦፕሬሽን የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተወካይ ስራ አስኪያጅ ቦሰና አባይ ደግሞ ኤርፎራ ጎንደር ስጋ ፋብሪካን መልሶ የማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።
የጥገናና የእድሳት ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ስራ አስኪያጅዋ ማሽን የማስገባት ስራ በመከናወኑን መቻሉን ገልጸዋል ።
አሁን ላይ ለ35 ቋሚ ስራ እና 50 ደግሞ ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል ። በቀጣይ ወደ ማምረት ሲገባ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል ።