Activity

የግብርናችን አዲሱ ገፅታ

የግብርናችን አዲሱ ገፅታ
★ በብርሀን ተሻለ ★
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በአመት አንድ ጊዜ፤ ለዚያው የክረምት ዝናብ እየተጠበቀ የሚደረግ የግብርና ስራ የሀገር ውስጥ ፍጆታን እንኳን ለማሟላት የማያስችል ከመሆኑ ባሻገር በምግብ እህል ራስን የመቻል ግባችንን የማይታሰብ ያደርገዋል፡፡

በመሆኑም የአመራረት ዘዴን ማዘመን ያስፈልጋል፡፡ ከተለምዶ የአመራረት ዘይቤ ወጣ ባለ መልኩ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ማዕከል ያደረገ የግብርና እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ግድ ይላል፡፡

ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግስት አርሶ አደሩ በአመት አንድ ጊዜ ከማምረት ወጥቶ የመስኖ ልማትን ተጠቅሞ በዓመት ሁለት እና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበትን ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል፡፡ የኩታ ገጠም የአመራረት ዘይቤ ተግባራዊ በመደረጉ በግብርናው ዘርፍ ውጤት ማስመዝብ ተችሏል፡፡

የበጋ መስኖ ልማት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጡም በላይ የገበያ ጉድለትን ለመሙላትም ከፍተኛ ሚና ዓለው፡፡

በኢኮኖሚው ውስጥ የሚስተዋለውን የገበያ ጉድለት ለመሙላት በተቀናጀ የአርሻ ልማት ዘዴ በርከት ያለ ምርት እንደሚያስፈልግ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የምርት ማሻሻያ ስልቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሀገራዊ ፍላጎታችንን በአገር ውስጥ ምርቶች መሸፈን እንችላለን፡፡ ይህን ማድረጋችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ልማት የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን መንገድ ጠራጊ ይሆናል፡፡

በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች እየተስፋፉ ያሉት የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ግብዓቶችን በስፋት ይጠቀማሉ፡፡

ከውጭ የሚመጡ ምርቶች በአገር ውስጥ የመተካት ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉ ለዚህ የሚውል የውጭ ምንዛሬን ወደሌላ ለማዛወር እድል የሚሰጥ በመሆኑ ቀጥታ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን ያፋጥናል፤ ብሎም የውጪ ምንዛሬ ጫና እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም ምርትና ምርታማነትን በቀጣይነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴዎችን እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃና የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ስራዎችን በማጠናከር ምርታማነት እንዲያድግ መስራት ይገባል

prosperity

Leave A Comment

Your Comment
All comments are held for moderation.